የሀገር ውስጥ ዜና

ኢሬቻ በድምቀት እንዲከበር ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተሠራ ነው – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

By Adimasu Aragawu

October 02, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፌደራል ፖሊስ የሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

ፌደራል ፖሊስ የኢሬቻ በዓላት አከባበርን በተመለከተ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ጋር ውይይት አካሂዷል። ‎ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ኃላፊነቱን እየተወጣ በመሆኑ አጠቃላይ ያለፉት ሁነቶች በመላው ሀገሪቱ በድምቀት ተጠናቀዋል።

በቀጣይም የሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ ሀርሰዲ የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ የፀጥታ ኃይል በማሰማራት ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።

የበዓላቱን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የፀጥታ ኃይሉ ከሕብረተሰቡ ጋር ትስስር ፈጥሮ እየሠራ መሆኑን አንስተዋል።

የኢሬቻ ባህልና እሴት ከሚፈቅደው ውጪ በማንኛውም ሁኔታ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን፣ ስለታማ፣ ተተኳሽና ተቀጣጣይ ነገሮችን ይዞ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ መምጣት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አሳስበዋል።

የበዓሉ ታዳሚዎችም ለፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን የፌደራል ፖሊስ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ ገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!