የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሰኞ ይካሄዳል

By Melaku Gedif

October 03, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሰኞ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

በዚህ መሰረትም የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን ÷ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በመጪው ሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!