የሀገር ውስጥ ዜና

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሯል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Mikias Ayele

October 04, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ አከባበር ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እጅግ በደመቀና ባማረ ሁኔታ ተጠናቅቋል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ ሀገራት ጎብኚዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች በታደሙበት በልዩ ሁኔታ ደምቆ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቅቋል ብለዋል።

በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት ያማረችው አዲስ አበባችን ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላው ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት መሆኗን ጠቅሰዋል።

በዓሉ እጅግ ባማረ፣ ደማቅና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት፣ በተለይም ለከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።