የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ ይኖርባታል – ፕሬዚዳንት ታዬ

By Adimasu Aragawu

October 06, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገራችን በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል በዛው ልክም አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ ይኖርባታል አሉ።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ይህንን ያሉት 6ኛውን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ህልውና መሰረት በሆኑት በሁለቱ ታላላቅ የውሃ ሀብቶች ዙሪያ መንግሥት ያልተቋረጠ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።

እስካሁን በተደረጉ ጥረቶች ሦስት ጉልህ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ÷ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አጋጥሞት የነበረውን ፈተናዎች በጥበብ በማለፍ ማጠናቀቅና በደመቀ ሥነ ሥርዓት ማስመረቅ መቻሉን ጠቅሰዋል።

አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ የተሸጋገረና ይህ ፍትሃዊ ጥያቄም በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ እያደገ የመጣ ቅቡልነት ማግኘት መቻሉን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በውጭ ሀገር ለእንግልትና ለችግር የተጋለጡ ዜጎች በክብር ወደ ሀገር የተመለሱ መሆናቸውንና ወደፊትም ይኸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው የልማት ግንባታ እንዲሳተፉ ጥረቶች መደረጋቸውንም ተናግረዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!