አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሳው እና የማኔጅመንት አባላት የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት ስራዎች መጎብኘታቸውን ገልጸው÷ በተደራጀ እና በተቀናጀ መልክ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ብለዋል።
ስምምነቱ በዋናነት በከተማችን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት የለሙ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ በዚህም የስቶክ ኦቨር ቱሪዝም ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ የከተማዋ አዲስ መለያ የሆነውን new face of Africaን ማስተዋወቅ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የአቪየሽን ደህንነትን ማረጋገጥ እና በከተማው የተለያዩ ማህበራዊና ሰው ተኮር ስራዎችን በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ እንደሆነ አመላክተዋል።
አየር መንገዱ ከተማ አስተዳደሩ በምሰራቸው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እና በኮሪደር ልማት ላይ ለነበረው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባዋ÷ የከተማ አስተዳደራችን ለስምምነቶቹ ተፈፃሚነት ከአየር መንገዱ ጋር ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ተቀራርቦ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!