አዲስ አበባ፣መስከረም 27፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነቀምቴ ከተማ ቢፍቱ ነቀምቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ45 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ለአገልግሎት በቅተዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በነቀምቴ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በከተማዋ የሚገኘውን ቢፍቱ ነቀምቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመለከቱ ሲሆን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የተገነባውን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መርቀው ለአገልግሎት አብቅተዋል።
የመማሪያ ክፍሎቹ በ45 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ሲሆን፤ ወጪውን የሸፈነው ፀሐይ ቃበታ ፋውንዴሽን መሆኑ ተገልጿል።
በገላና ተስፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!