አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኩባ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የነበሩት አየለ ሊሬ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የስራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
አምባሳደር አየለ ሊሬ ለረጅም ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በባለሙያነትና በተለያዩ የአመራር ደረጃ አገልግለዋል።
አምባሳደሩ እስከ ህልፈታቸው ድረስ በኩባ ሀቫና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተጨማሪም ባርባዶስ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ኒኳራጓ፣ ሴንት ቪንሰንት እና ግራናሪስ፣ ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ እንዲሁም ባሃማስን ሸፍነው ሀገራቸውን በታማኝነት እና በላቀ ብቃት ያገለገሉ ነበሩ፡፡
አምባሳደር አየለ ሊሬ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!