ቴክ

የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት ለሦስት የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች ተበረከተ

By Adimasu Aragawu

October 07, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2025 የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት ለሦስት የኮምፒውተር ሳይንትስቶች ተበርክቷል።

ጆን ክላርክ፣ ሚኬል ኤች ዲቮሬት እና ጆን ኤም ማርቲንስ የኖቤል ሽልማቱን ያሸነፉ የኮምፒውተር ምህንድስና ባለሙያዎች ሲሆኑ÷ ሽልማቱን ያገኙት ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥን ጠንካራ ኮምፒውተሮችን በመፍጠር ሂደት በሰሩት ስራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኖቤል ኮሚቴ በአሁኑ ዘመን ሞባይልን ጨምሮ ካሜራ የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች የዚህ ዘርፍ ጥገኛ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የዘርፉ የኖቤል አሸናፊዎች በስዊዲን ሮያል የሳይንስ አካዳሚ ይፋ የተደረገ ሲሆን÷ በካምብሪጅ ዩናይትድ ኪንግደም የተወለዱት የሽልማቱ አሸናፊ ጆን ክላርክ (ፕ/ር) የህይወቴ ትልቁ ሽልማት ነው ብለዋል፡፡

ለሦስቱ አሸናፊዎች 872 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸውም ተጠቁሟል።

የተመራማሪዎቹ ግኝት ለዘርፉ ትልቅ ፋይዳ ያለውና ምርምሩ ከፈረንጆቹ 1980 በኋላ ትልቁ እንደሆነ የቢቢሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ምርምሩ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን አሁን ከደረሰበት ደረጃ ከፍ በማድረግ እጅግ ረቂቅ እና ዘመናዊ እንዲሆን እንደሚያስችልም ተገልጿል፡፡

በአቤል ነዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!