የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቦሌ ቅርንጫፍ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ስራ አስጀመሩ

By Adimasu Aragawu

October 08, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቦሌ ቅርንጫፍ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሕዝቡ ሲጠይቅና ቅሬታ ሲያቀርብበት የነበረውን የአገልግሎት ዘርፍ ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

ለዚህም በመዲናዋ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተጨማሪ በሌሎች ክፍለ ከተሞች የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ የተመረቀው የቦሌ ቅርንጫፍ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

በመዲናዋ አሁን ላይ 107 አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ተደርገው ሕዝቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ መደረጉን ጠቁመዋል።

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በጥራትና ቴክኖሎጂ የተሻለ መሆኑን የጠቆሙት ደግሞ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ናቸው።

የቦሌ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለስድስት ወለል ህንጻ በአራት ወራት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ አሁን ላይ 12 ተቋማት በድምሩ 96 አገልግሎቶችን መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል።

በታሪኩ ለገሰ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!