አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 9ኛ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት ከጊኒ ቢሳው ጋር ያደርጋል፡፡
ከ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መርሐ ግብር ለማሟላት ነው ጨዋታውን የሚያካሂደው፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በማጣሪያው ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ሲያሸንፍ ÷ በሶስቱ አቻ እንዲሁም በአራቱ ደግሞ ተሸንፏል፤በዚህም በ6 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ጊኒ ቢሳው ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች 10 ነጥብ በመሰብሰብ በምድቡ 4ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ በሩዋንዳ ኪጋሊ አማሆሮ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ምድቡን ግብጽ በ20 ነጥብ ስትመራ ቡርኪነፋሶ በ15፣ ሴራሊዮን በ12፣ ጊኒ ቢሳው በ10፣ ኢትዮጵያ በ6 እንዲሁም ጂቡቲ በ1 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!