አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ቢሊየነር ሆኗል፡፡
የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የተጣራ የሀብት መጠን 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር መድረሱን የብሉምበርግ ዘገባ አመላክቷል፡፡
ተጨዋቹ ከሳዑዲው ክለብ አል ናስር የሚያገኘው 300 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ እና ከሌሎች አጋሮች የሚያገኘው ገቢ ያለውን የሀብት መጠን ከፍ እንዳደረገለትም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብሉምበርግ የቢሊየነሮች ደረጃ ውስጥ መካተት የቻለ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ተጨዋች መሆን ችሏል።
ሮናልዶ ከፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምንጊዜም ምርጡ ተጨዋች በመባል በትናንትናው ዕለት የክብር ሽልማት እንደተሰጠው ይታወሳል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!