የሀገር ውስጥ ዜና

የሸገር ከተማ በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጠ

By Adimasu Aragawu

October 09, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸገር ከተማ አስተዳደር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከ500 ነጥብ በላይ በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና ሰጠ።

ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የግልና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ተማሪዎቻቸው ነው የማበረታቻ ዕውቅና የሰጠው።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊራኪያ ካሣሁን የግልና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውጤታማ ተማሪዎችን እንዲያፈሩ የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

ቢሮው የትምህርት ቤቶቹን ተደራሽነት በማስፋፋት የግልና የመንግሥት ት/ቤቶች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በመደገፍ የበኩሉን አስተዋጽዖ እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በዚህም ትምህርት ቢሮ በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከ500 ነጥብ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ 57 ተማሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን÷ 6 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተጨማሪ የገንዘብ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል።

በታሪክ አዱኛ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!