ቢዝነስ

ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማፋጠን የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታን እያስፋፋች ነው – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

October 09, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማፋጠንና የገቢና ወጪ ምርትን ለማጓጓዝ የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታን እያስፋፋች ነው አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)።

ኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከዋናው ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ጋር የሚያገናኝ የባቡር ሃዲድ ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀመሯል።

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ወደ ትግበራ ምዕራፍ እየገባች ትገኛለች፡፡

ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ያለመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታሰብ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፥ ለዚህም ለባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዛሬ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት የባቡር ሃዲድ ግንባታ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ በራስ አቅም የተመሰረተ ብልፅግናን የማረጋገጥ ውጥኗ ፍሬ እያፈራ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው፥ ተቋሙ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የባቡር መስመር፣ የፈጣን መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታዎችን በስፋት ለማከናወን ግብ መያዙን ጠቁመዋል።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የሚከናወነውን የባቡር መስመር ግንባታ በስድስት ወራት ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡

ኤ ኤም ጂ ሆልዲንግስ በወጪ ንግድ፣ በአምራችና አገልግሎት ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ሰባት ኩባንያዎችን እንዲሁም የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ 40 ፋብሪካዎችን በውስጡ መያዙ ተጠቁሟል፡፡

በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ላይ የሚገኘው የኢንዱስትሪ ፓርኩ፥ በተለያዩ ምርቶች ላይ እሴትን ጨምሮ ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

የባቡር መሰረተ ልማቱ ግንባታ እያደገ ያለውን የኢንዱስትሪ ፓርኩን የወጪ ንግድ የሚያሳልጥ ቀልጣፋ የሎጅስቲክስ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችለዋል ነው የተባለው።

በመራኦል ከድር