የሀገር ውስጥ ዜና

የዲጂታል አገልግሎትን በማስፋት ለልማት እቅዶች መሳካት በትኩረት ይሰራል – ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ

By Yonas Getnet

October 09, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል የዲጂታል አገልግሎትን በማስፋት ለልማት እቅዶች መሳካት በትኩረት ይሰራል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ።

በዲጂታል እቅድ ክትትልና ግምገማ ሥርዓትና በልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ የዲጂታል አገልግሎትን በማስፋት ለልማት እቅዶች መሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመናዊና የተሳለጠ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ካለው ፋይዳ በተጨማሪ ሥራዎችን ከርቀትና ከየትኛውም ቦታ ሆኖ መምራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የምክክር መድረኩም በክልሉ ያለውን የመረጃ አያያዝ ሥርዓትና በዲጂታል የእቅድ ክትትልና ግምገማ ረገድ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ያቃልላል ነው ያሉት፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመከታተልና ስኬታማ ለማድረግ ዘመኑ ያፈራቸውን የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

የዲጂታል እቅድ ክትትልና ግምገማ ሥርዓትን ወደ ክልል በማውረድ የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን ማሳለጥ የምክክር መድረኩ አላማ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!