የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ተጀመረ

By Melaku Gedif

October 09, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያን ንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡

ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ተልከዋል፡፡

በቅድስት አባተ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!