የሀገር ውስጥ ዜና

የመሪዎች ጉባኤ ሀገራት ከፉክክር ይልቅ በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ እና አብሮ የማደግ እሴት የሚዳብርበት ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ

By Adimasu Aragawu

October 09, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 24ኛው የኮሜሳ መሪዎች ጉባኤ ሀገራት ከፉክክር ይልቅ በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ እና አብሮ የማደግ እሴት የሚዳብርበት ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሳተፉበት 24ኛው የኮሜሳ መሪዎች ጉባኤ በዛሬው ዕለት በኬንያ ናይሮቢ ተካሂዷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የመሪዎች ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ÷ ጉባኤው ሀገራት ከፉክክር ይልቅ በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ እና አብሮ የማደግ እሴት የሚዳብርበት መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ያለው የዲጂታል ሥርዓት የእሴት ሰንሰለቱን የተሻለ ደረጃ በማድረስ በኩል ሀገራት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማሳየት የሚያስችሉ ልምዶችን የተለዋወጡበት መድረክ እንደሆነ አንስተዋል።

ኮሜሳ ከተቋቋመ ረጅም ጊዜ የሆነና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ሊፈጠር የሚገባውን የንግድ ትስስር ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ብዙ ርቀት የሄደ ተቋም መሆኑንም ጠቁመዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!