አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በአገልግሎት አሰጣጥና ዙሪያ ከወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት÷የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ረገድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በወረዳዎች የማሕበረሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ በማሻሻል ፍትሃዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡
ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና በማረም መልካም አስተዳደር ከማስፈን እንዲሁም የልማት ሥራን ከማፋጠን ጎን ለጎን ለጸጥታ ጥበቃ ሥራ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ በክልሉ በኮሪደር ልማት የተመዘገበውን ውጤት ለማስፋት ይሰራል ነው ያሉት፡፡
የኮሪደር ልማት ሥራውን በውስጥ ለውስጥ መንገዶች በማስፋት ከዋና መንገዶች ጋር ለማገናኘት እንደሚሰራ መናገራቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!