አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።
በኩሪፍቱ አፍሪካ ሪዞርት እየተካሄደ ባለው ፌቲቫል ከመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ለማሳያነት የተመረጡ የ31 ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች በምግብ ፌስቲቫሉ ላይ ቀርበዋል።
ፌስቲቫሉ በዋናነት ባህል እና ባህላዊ ምግቦችን ማስተዋወቅ፣ ወደ ገበታ እንዲመጡ ማድረግ፣ የእርስ በርስ ትውውቅን መፍጠር፣ የሀገር ገጽታ መገንባት እና የምግብ ቱሪዝምን የማሳደግ ፋይዳዎች ዓላማ ያደረገ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የእናቶችን ሀገር በቀል እውቀት ወደ ቀጣዩ ትውልድ የማሻገር የዚህ የምግብ ፌስቲቫል ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ምግቡን ያዘጋጁ እናቶች፣ የየብሔረሰቦቹ ተወካዮች፣ ሆቴሎች እና የተለያዩ ተቋማት እየተሳተፉበት ይገኛል።
በቅድስት ብርሃኑ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!