ስፓርት

በቺካጎ ማራቶን ሃዊ ፈይሳ አሸነፈች

By abel neway

October 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ47ኛው የቺካጎ ማራቶን አትሌት ሀዊ ፈይሳ አሸንፋለች፡፡

አትሌት ሀዊ ፈይሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መገርቱ አለሙ ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡