አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተከብሯል።
በጽ/ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ፈይሳ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አባቶች በደም፣ በአጥንትና በህይወት መስዋዕትነት ያቆዩትን ድል የምናከብርበት መለያችን ነው ብለዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ሠንደቅ ዓላማችን ዳግም በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲታይ የተደረገበት ዓመት መሆኑ የዘንድሮን አከባበር ልዩ ያደርገዋልም ነው ያሉት።
ትውልዱ ሌሎች ሀገራዊ ስኬቶችን ለመድገም ዳግም ቃሉን የሚያድስበት ዕለት መሆኑም ተጠቅሷል።
የዘንድሮው ሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!