አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች መከበር ጀምሯል።
በዓሉ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የሠንደቅ ዓላማ ቀን አሁን ላይ በኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነት በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች መከበር ጀምሯል፡፡
4፡30 ሰዓት ላይም በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።
በተጨማሪም በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ የመፈጸም መርሐ ግብር እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!