የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

By Melaku Gedif

October 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው በዓል ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ቀደምት አባቶቻችን ያረጋገጡትን ሉዓላዊነታችንን ለማጽናት መክፈል የሚገባንን ዋጋ ሁሉ መክፈል ይጠበቅብናል ብለዋል።

በአርበኝነት ስሜት ከድህነት ለመውጣት አንድነታችንን ጠብቀን ጥረታችንን ከቀጠልን አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ከፍታን ወደ ላቀ ደረጃ እናደርሳለን ሲሉም ገልጸዋል።