የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

By Adimasu Aragawu

October 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች በቦንጋ ከተማ ተከብሯል።

“ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ በተከበረው በዓል ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ እንደ ሠንደቅ ዓላማ ያሉ የጋራ እሳቤ የሚያሰርጹ፣ አንድነታችን እና አብሮነታችን የሚያስተሳስሩ የጋራ ጉዳዮችን በየጊዜው መዘከር እና ከፍ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን በጋራ ለስኬት ያበቁት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንደ ሠንደቅ ዓላማ የጋራ ገዥ ትርክት የሚገነባ የወል ሀብት እንደሆነም ጠቅሰዋል።

የአሁኑ ትውልድ የሀገራችን የነጻነት ምልክትና የሉዓላዊነታችን መለያ የሆነውን ሠንደቅ ዓለማ ክብር እና ልዩ ቦታ በመስጠት በየጊዜው መዘከር እና ከፍ ከፍ ማድረግ ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!