አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ኪልባቲ ረሱ ኮናባ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ500 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
የኮናባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ያህያ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በወረዳው በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
በዚህም በአጠቃላይ በ517 ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አንስተው÷ ኡሩሁና ኤደጋሃኑ በተባሉ ቀበሌዎች 74 የውሃ ጉድጓዶች ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከአስር ሄክታር በላይ የእርሻ መሬትን ከጥቅም ውጭ እንዳደረገና በሁለት መስጂዶች ላይ እንዲሁም ስምንት ክፍሎች ባለው ትምህርት ቤት ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥ በወረዳው ከ3 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀሉንም ጠቁመዋል።
በአካባቢው አሁንም ድረስ የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክቶች መኖራቸውን ገልጸው÷ ማህበረሰቡ ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች በመውጣት ራሱን እንዲጠብቅም አሳስበዋል።
በአደጋው ተጎጂ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ እና ፈጣን ምላሽ በመስጠት መልሶ ለማቋቋም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው አመላክተዋል።
በያሲን ኑሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!