አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ያተኮረው 10ኛው የአፍሪካ እንስሳት ዓውደ ርዕይ ከጥቅምት 20 እስከ 22/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር፣ ፕራና ኢቨንትስና ኤክስፖ ፒም በጋራ የሚያዘጋጁትን ዓውደ ርዕይ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በሁነቱ ላይ ከ14 ሀገራት በላይ የተውጣጡ የዘርፉ ተዋንያን የሚሳተፉ ሲሆን፥ ከ5 ሺህ በላይ ጎብኚዎች አውደ ርዕዩን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዓውደ ርዕዩ ከተለያዩ ሀገራት የዘርፉ ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ የሥራ ግንኙነትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
በሃይማኖት ወንድራድ