የሀገር ውስጥ ዜና

ንጋት ሐይቅ በማስተር ፕላን አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያሳድጋል

By Adimasu Aragawu

October 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሐይቅ በማስተር ፕላን አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ያሳድጋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የንጋት ሐይቅ ረቂቅ ማስተር ፕላን ላይ የባለድርሻዎች የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ ንጋት ሐይቅ በማስተር ፕላን መመራቱ ያለውን አቅም አሟጦ ለመጠቀም ያስችላል።

በአሁኑ ወቅት በሐይቁ ላይ በዓሣ ማምረት ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰው፥ ይህንን እና ሌሎች የሐይቁን በረከት ለመጠቀም የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

በመሆኑም የንጋት ሐይቅ በማስተር ፕላን እንዲመራ የተጀመረው እንቅስቃሴ በዓሣ ልማት፣ በቱሪዝም እና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሻለ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ያስችላል ነው ያሉት።

የረቂቅ ማስተር ፕላን ዝግጅት ክልሉን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ መሆኑ የንጋት ሐይቅ ኢኮኖሚያዊ አቅምን አሟጥጦ ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል።

በሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው በአፍሪካ 4ኛው ግዙፉ የንጋት ሐይቅ ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉትና ከ74 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዩብ በላይ ውሃ የያዘ ነው።

በአቢይ ጌታሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!