አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ የቀበሌ አደረጃጀት ለገጠር ሕብረተሰብ በቅርበት እየተሰጠ ያለውን መንግሥታዊ አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ።
በክልሉ አዲስ ለተደራጁ የቀበሌ መዋቅሮች 6 ሺህ 800 የሞተር ብስክሌቶች ተከፋፍለዋል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የክልሉ መንግሥት በመዋቅሮቹ የሚሰጠውን የሕዝብ አገልግሎት ለማሳለጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በተለይም የአገልግሎት አሰጣጡን የማዘመንና በቴክኖሎጂ የመደገፍ፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የማድረግ ሥራ እያከናወነ ነው ብለዋል።
በክልሉ የገጠሩ ሕብረተሰብ የተሻለ መንግሥታዊ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ የቀበሌ መዋቅር በማደራጀት ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸው÷ አደረጃጀቶቹ የተፈለገውን አገልግሎት በመስጠት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
አደረጃጀቱን በሰው ኃይል ማብቃትና በሎጂስቲክስ ማጠናከር ላይ በትኩረት እየሰራን ነው፤ ይህም ሕዝባችን የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ እያስቻለ ነው ብለዋል።
በዛሬው ዕለት የሞተር ብስክሌቶች ለቀበሌ መዋቅሩ ስናስረክብ ለሕብረተሰቡ ይበልጥ በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!