ስፓርት

ስዊድን አሰልጣኟን አሰናበተች

By Adimasu Aragawu

October 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ጆን ዳህል ቶማሰን ከስዊድን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ፡፡

የስዊድን ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ እያስመዘገበ የሚገኘውን ውጤት ተከትሎ ነው ዋና አሰልጣኙን ያሰናበተው፡፡

ስዊድን በ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ካደረገቻቸው አራት ጨዋታዎች በሦስቱ ተሸንፋ በአንዱ አቻ ተለያይታለች፡፡

በዚህም ስዊድን አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የምድቡ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ስዊድን አሌክሳንደር ኢሳክ፣ ቪክቶር ዮኬሬሽ፣ ኩልሴቭስኪ፣ ኢላንጋ እና ቪክቶር ሊንደሎፍን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በስብስቧ ብትይዝም ደካማ እንቅስቃሴ እያረገች ትገኛለች፡፡

የስዊድን ብሔራዊ ቡድን ወደ 2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!