ስፓርት

ዲዮንግ በባርሴሎና ለተጨማሪ አምስት ዓመታት የሚያቆየውን ስምምነት ፈረመ

By Yonas Getnet

October 15, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርሴሎናው አማካይ ቦታ ተጨዋች ፍሬንኪ ዲዮንግ በክለቡ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።

በ2019 ከአያክስ የካታሎኑን ቡድን ባርሴሎና የተቀላቀለው ፍሬንኪ ዲዮንግ በቡድኑ የአማካይ ቦታ ላይ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያሳይ ቆይቷል።

እስከ 2029 ድረስ የሚያቆየውንን አዲስ ውል የፈረመው ዲዮንግ በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ የነበረ ቢሆንም ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ከባርሴሎና ጋር ለመቀጠል መወሰኑ ይታወሳል።

ኔዘርላንዳዊው የ28 ዓመቱ ተጨዋች ለባርሳ ከ200 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን÷ በሜዳው ላይ በሚያሳየው የተረጋጋ የኳስ ቁጥጥር፣ ቅብብል እና ድንቅ ብቃት ይታወቃል።

የክለቡ ኃላፊዎች ስምምነቱ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት የረጅም ጊዜ ዕቅዳቸው አካል በመሆን ከእርሱ ጋር በመቀጠላቸው ደስተኞች እንደሆኑ ገልጸዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!