የሀገር ውስጥ ዜና

ፋኦ ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ እውቅና ሰጠ

By Adimasu Aragawu

October 15, 2025

‎አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ዘላቂ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀም በሚል ዘርፍ እውቅና ሰጠ።

በተባበሩት መንግሥታት ስር የሚገኘውና መቀመጫውን ጣሊያን ሮም ያደረገው ፋኦ ለኢትዮጵያ የሰጠውን የእውቅና ሽልማት ኢትዮጵያን ወክለው የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተቀብለዋል። ‎ ፋኦ ከዚህ ቀደም ‎በምግብ ዋስትና፣ በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦትና በስንዴ ምርት ፈጣን አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት ቁርጠኝነት ‎የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ መሸለሙ ይታወሳል።

በፍሬህይወት ሰፊው

በፍሬህይወት ሰፊው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!