አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም የገንዘብ ሥርዓት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ዘላቂ ልማት ታሳቢ ያደረገ እና ፍትሃዊ እንዲሆን ጥሪ አቅርባለች፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን እየተካሄደ በሚገኘው 114ኛው የቡድን 24 ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስትሊና ጆርጂየቫ እና የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቤርዴን ጨምሮ የአባል ሀገራቱ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ፥ ለታዳጊ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የዓለም የገንዘብ ሥርዓት ሊኖር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የቡድን 24 አባል ሀገራት በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ መሰረት የዕዳ ሽግሽግ ሒደት ተግባራዊ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥሪ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ ፥ በዚህ ረገድ ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል፡፡
የዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተሮች በዚሁ ወቅት ተቋሞቻቸው ከቡድን 24 ስብስብ ጋር የሚያከናውኗቸውን ተግባራት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
በአባል ሀገራቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አድንቀው ፥ ዘላቂና አካታች ልማት እንዲሁም የተረጋጋ የፋይናንስ ሥርዓትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ማሻሻያዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!