ቢዝነስ

ብሔራዊ ባንክ አይ ኤም ኤፍ በአባል ሀገራት ድርሻ ላይ ያደረገው ማሻሻያ እንዲፋጠን ጠየቀ

By Adimasu Aragawu

October 17, 2025

‎አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አይ ኤም ኤፍ በአባል ሀገራት ድርሻ ላይ ያደረገው 50 በመቶ ማሻሻያ እንዲፋጠን የባንኩ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ጠየቁ።

ከ2025ቱ የዓለም ባንክ እና የአይ ኤም ኤፍ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን የአፍሪካ ግሩፕ ኮንስትቱየንሲ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡

እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ብሔራዊ ባንክ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በአባል ሀገራት ድርሻ ላይ ያደረገውን 50 በመቶ ጭማሪ በአዎንታዊ ጎኑ ይመለከተዋል ብለዋል።

የድርሻ ማሻሻያው የዓለም አቀፍ የፋይናንሺያል ሴፍቲኔትን ለማጠናከር እና ለአባል ሀገራት የሃብት አቅርቦትን ለማጎልበት አዎንታዊ እርምጃ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ተቋሙ ያደረገው የድርሻ ማሻሻያው እንዲፋጠንም የጠየቁት እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)÷ የድርሻ ጭማሪውና ፈጣን አተገባበሩ ተቀባይነት ያለው እንደሆነና የድርሻ ማስተካከያ አጣዳፊነት ግን ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የታዳጊ አባል ሀገራት ድርሻን መጠበቅ ላይ እየታየ ያለውን ስምምነት በማድነቅ አሁን ባለው ማዕቀፍ ታዳጊ ሀገራት ያላቸውን ዝቅተኛ ውክልና መፍታት አስፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ፍትሃዊ፣ ሚዛናዊና ሁሉን አቀፍ የሆነ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓትን ለማረጋገጥ ዝቅተኛ ውክልና ያላቸው ሀገራት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!