የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዲንሾ ሎጅ እና የጌሴ የሳር ምድርን ጎበኙ

By Abiy Getahun

October 17, 2025

‎አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሌ ዞን በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ እና ከባቢውን እንዲሁም የጌሴ የሳር ምድርን ጎብኝተዋል።

ከአዲስ አበባ 400 ኪሎ ሜትሮች ርቀት በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር ስኴር በላይ ስፋት ላይ ይገኛል።

ፓርኩ በኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ያለውን ተራራ ጨምሮ አስደናቂ የመልክዓ ምድር ገጽታዎችን፣ የዱር እንስሳትን፣ ደኖችን፣ የሳር ምድሮችን እና የተለያዩ የተክል አይነቶችን በመያዙ “የተለያየ ዓለም በአንድ ፓርክ” ተብሎ ለመጠራት የበቃ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጉብኝታቸውን ያደረጉት ከቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡