አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል፡፡
ለራይላ ኦዲንጋ አስከሬን ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ በርካታ መሪዎች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት የክብር ሽኝት ተደርጓል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ኬንያውያንም በስታዲየሙ ተገኝተው ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ያላቸውን ክብር እና አድናቆት በማሳየት በህልፈታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡
ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም በርካታ ኬንያውያን የራይላ ኦዲንጋን ምስል የያዘ ቲ ሸርት በመልበስ የኬንያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው አደባባይ ወጥተዋል፡፡
የአስከሬን የክብር ሽኝት ከተከናወነ በኋላ ስርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡