ቢዝነስ

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከቻይና ፒፕልስ ባንክ ገዥ ጋር ተወያዩ

By Abiy Getahun

October 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከቻይና ፒፕልስ ባንክ ገዥ ፓን ኮንግሼንግ ጋር ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የኢትዮ ቻይና የፋይናንስ ትብብር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆን፤ የድንበር ተሻጋሪ የንግድ ግንኙነት በሚጠናከርበት እና የዕዳ ሽግሽግ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት አካሂደዋል።

የሁለቱ ሀገራት ማዕከላዊ ባንኮች እና የገንዘብ ተቋማት ንግድ እና የኢንቨስትመንት ፍሰትን እንዲያሳድጉ ለማስቻል ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተነጋግረዋል።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የፋይናንስ ዘርፍን ጨምሮ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ስትራተጂካዊ አጋርነት አጠናክራ ለማስቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

አጋርነቱ እየተከናወነ ከሚገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር በተናበበ መልኩ የሚከናወን መሆኑንም ተናግረዋል።

የሀገራቱን ዘላቂነት ያለው የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማስቀጠል የሚያስችል የቴክኒክ ውይይት እና ትብብር እንደሚቀጥል ሁለቱ ወገኖች ተስማምተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!