አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ነው አለ፡፡
ቢሮው በእናቶች፣ ህጻናት እና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት ዘርፍ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከወረዳና ዞን አመራሮች ጋር ተወያይቷል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ በወቅቱ እንዳሉት÷ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
ጥራት ያለው የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በተለይም የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በግብአት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰው ሃይል ማሟላት ላይ በስፋት በመስራት ህብረተሰቡ ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የህጻናት ክትባት፣ የድህረና ቅድመ ወሊድ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ያለውን አቅም በአግባቡ በመጠቀም እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
በያሲን ኑሩ