አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በመምከር ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመሻት የሁላችንም ጥረት፣ ትብብርና ተሳትፎ ያስፈልጋል አሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር)፡፡
ኮሚሽኑ በሆሳዕና ከተማ “የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ሚና እና አስተዋጽኦ ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሃሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ መምከር ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የወደፊት እጣ ፋንታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው÷ ይህንን እድል መጠቀም ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን አንስተዋል።
በሂደቱ በተለይም የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ለስኬታማነት መሰል የውይይት መድረኮች በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የሁሉም ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለተግባራዊነቱ በጋራ መስራት አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በመምከር ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመሻት የሁላችንም ጥረት፣ ትብብርና ተሳትፎ ያስፈልጋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በመድረኩ ላይ ከሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች በተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲ ምክር ቤት ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!