ፋና ስብስብ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያስገነባው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አቀፍ ሬዲዮ ጣቢያ ተመረቀ

By Yonas Getnet

October 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያስገነባው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍ ሬድዮ ጣቢያ በዛሬው ዕለት ተመርቋል። ‎ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደገላ ኤርጌኖ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ‎ሬዲዮ ጣቢያው ዩኒቨርሲቲው የሚሰራቸውን ሥራዎች እንዲሁም የአካባቢውን ማህበረሰብ ባህልና እሴት ለሌሎች ለማስተዋወቅ ፋይዳ አለው። ‎ ‎ዩኒቨርሲቲው በምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እንዲሁም በመማር ማስተማር ዘርፉ እያከናወነ ያለውን ተግባር ጨምሮ አካባቢያዊና ዓለም አቀፍ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋልም ነው ያሉት። ‎ ‎የሬዲዮ ጣቢያ ስቱዲዮ ዘመኑን የሚመጥን የሚዲያ ቴክኖሎጂን ያሟላ መሆኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ በሚዲያው እንዱስትሪ ያካበተውን አቅም የሚያሳይ እንደሆነና ተቋሙ በዘርፉ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይነት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ‎ ‎የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዶኒያስ ወ/ዓረጋይ በበኩላቸው÷ የሬዲዮ ጣቢያው ፋና በሚዲያ እንዱስትሪ ያካበተውን ልምድ ወደ ማህበረሰብ የማውረድ ሥራን እየሰራ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። ‎ ኮርፖሬሽኑ በሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝና በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎች መሰል የማስፋፋት ስራዎችን እንደሚሰራ አመላክተዋል። ‎ ‎ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያለው የአብሮነት ስራ እንደሚቀጥል እና የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት የሚረዱ ሥልጠናዎችም እንደሚሰጡ አቶ አዶኒያስ ተናግረዋል። ‎ በ‎ፍሬው አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!