ስፓርት

ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ

By Yonas Getnet

October 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሊጉ 8ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ነው ያሸነፈው።

በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ምንም ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት ቼልሲዎች በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ተጫዋቾችን በመቀየርና በጨዋታው ብልጫ በመውሰድ 3 ነጥብ አሳክቷል።

በጨዋታው የቼልሲን ማሸነፊያ ግቦች ጆሽ አቼምፖንግ፣ ፔድሮ ኔቶ እና ሪስ ጀምስ አስቆጥረዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ በተመሳሳይ ምሽት 11፡00 ላይ ብራይተን ከኒውካስል፣ በርንሌይ ከሊድስ ዩናይትድ፣ ክሪስታል ፓላስ ከበርንማውዝ፣ ማንቼስተር ሲቲ ከኤቨርተን እና ሰንደርላንድ ከወልቭስ ሲገናኙ ምሽት 1:30 ላይ ደግሞ ፉልሃም ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!