የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By Melaku Gedif

October 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት፥ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት በነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እረፍት በጥልቅ አዝኛለሁ ብለዋል፡፡

በመልካም አበርክቷቸው ሁሌም የሚታወሱ መሆኑን ገልጸው ÷ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡