አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ረትቷል።
የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ክንዱ ባየልኝ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤልና ሰቲ ኦሴ ሲያስቆጥሩ ÷ የሃድያ ሆሳዕናን ብቸኛ ግብ ደግሞ ጫላ ተሺታ ከመረብ አሳርፏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ምድረ ገነት ሽረ መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የምድረ ገነት ሽረን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ዳንኤል ዳርጌ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን ከአዳማ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!