የሀገር ውስጥ ዜና

አንድ ሰው ወደ ታሪክ መመልከት ያለበት ለትምህርት ብቻ ነው  – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Yonas Getnet

October 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከታሪክ ጋር ያለን ጸብ ወደ ፊት መራመድ እንዳንችል በእጅጉ ይዞናል፤ ሰው ወደ ኋላ መመልከት ያለበት ለትምህርት ብቻ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት፤ ሶፍ ዑመር ዋሻን ለመጀመሪያ ጊዜ በተመለከቱበት ወቅት ይሄንን የሚያክል ኃብት እያለ መዘንጋቱ እንዳስቆጫቸው፣ እንዳበሳጫቸው እና እንዳሳዘናቸው አስታውሰዋል።

የሶፍ ዑመር ዋሻ ርዝመቱ፣ የአርክቴክቸር ጥልቀቱ፣ የድንጋዩ ብዛት እና በውስጡ ያሉ እና ያልገቡን ነገሮች በጣም ብዙ ናቸው ሲሉ ገልጸው፤ ይህንን ዋሻ በጀት መድቦ ለመስራት ቢታሰብ ብዙ ጊዜ እና ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ነው ብለዋል።

ከኋላ ጋር ያለን ጸብ ወደ ፊት እንዳንራመድ በእጅጉ ይዞናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አንድ ሰው ወደ ኋላ መመልከት ያለበት ለትምህርት ብቻ መሆኑን አሳስበዋል።

ከዚያ ያለፈው ንትርክ እና ትናንት ውስጥ መኖር ዛሬን እንዳንሰራ ነገን አርቀን እንዳንመለከት የሚዳርግ ነው ብለዋል።

ከታሪክ ጋር ጸብ አይኑር የሚለው እሳቤ በሶፍ ዑመር ዋሻ የተጀመረ እንዳልሆነ ጠቅሰው፥ የአክሱም ሃውልትን ለማስጠገን እና ለማጠናከር ስራዎች ተጀመረው እንደነበር እና በላሊበላ ደግሞ ስራ መጀመሩን አንስተዋል።

አያይዘውም የፋሲል ቤተ መንግስትን ወደነበረበት ወይም ከዚያ በተሻለ ተውቦ እንዲሰራ መደረጉን እና የሶፍ ዑመር ዋሻም የዚሁ ሌላኛው ምሳሌ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሃላላ ኬላ የተሞከረው ስራ ታሪኮቻችን በየትኛውም ጫፍ ቢሆኑ የእኛው ስለሆኑ መጥፋት የለባቸውም፤ ከትናንት ጋር ስንጨቃጨቅ ዛሬን ሳንሰራ ትውልድ ልመናን እየተቀባበለ መሄድ የለበትም የሚል ጽኑ ዕምነት በመኖሩ ነው ሲሉ አመልክተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!