አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሰፊ ቅርስ እና ሃብት ያላት ኢትዮጵያ ተራበች፤ ተቸገረች ሲባል ለምንድነው ብለን አለመነሳታችን የሚያስቆጭ ነው አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ባሌን የተመለከተ አንድ ኢትዮጵያዊ እንዴት ይህ ሁሉ ሃብት እያለን ተቸገርን በሚል ከመልስ ይልቅ ጥያቄ ይጠይቃል ብለዋል።
የኛ ድህነት ያለመፈለግ ነው ወይስ የመነፈግ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የመደመር መንግስት መጽሐፍ ‘የዓባይን ልጅ ለምን ውሃ ጠማው’ ሲል መጠየቁን አስታውሰው፥ ባሌ የሚመጣ ሰውም ይህ ሁሉ ሃብት እያለን ለምንድነው የተቸገርነው የሚል ጥያቄ ማንሳቱ የማይቀር መሆኑን ጠቅሰዋል።
የትልቅ ሃብት ባለቤት ሆነን እስከዛሬ መቸገራችን ለምን ብሎ የሚያስጠይቅ ነው ብለዋል።
በጉብኝቱ ድሃው አስተሳሰባችን ነው ወይስ ሃገራችን ናት ብዬ ጠይቄአለሁ ያሉት አማካሪ ሚኒስትሩ፥ እንደ ሃገር ያሉንን ሃብቶች አለመጠቀማችን ሁላችንንም ቁጭት ውስጥ ይከታል ነው ያሉት።
ባሌ ዞንን ብቻ ማየት ለምን እስከዛሬ ድሃ ተባልን የሚል ቁጭት ይፈጥራል ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ብዙ ሃብት እንዳላት መረዳት እንደሚቻል አንስተው፥ ይህ ትውልድ የሚቀየረው እነዚህን የቁጭት ጥያቄዎች በመመለስ ነው ብለዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!