የሀገር ውስጥ ዜና

በባሌ እየተከናወነ የሚገኘው የልማት ሥራ ለሌሎች አካባቢዎች አርአያ የሚሆን ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

By Yonas Getnet

October 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሌ ዞን እየተከናወነ የሚገኘው የልማት ሥራ ለሌሎች አካባቢዎች አርአያ የሚሆን ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር መክረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በአካባቢው በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ ማየት መቻል ለሌሎች ሥራዎች የሚያበረታታ ነው ።

ጉብኝቱ ካለፉት ጊዜያት አንጻር አሁን ላይ እንደሃገር ወደፊት ረጅም ርቀት መሄድ መቻላችንን የሚያመላክት ነው ሲሉ አንስተዋል።

ያለፉት ዓመታት በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለኢትዮጵያውያን የእድገት እና የለውጥ ተስፋ የታየበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ከተጀመሩት ሥራዎች በላይ በኢትዮጵያ ትላልቅ ልማቶች እንደሚተገበሩ ጠቁመው÷ ማሕበረሰቡን ዘርፈ ብዙ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚከናወነው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በሶስና አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!