አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ፡፡
የክልሉ የአስፈፃሚ አካላት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል።
ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ ግምገማው የአስፈፃሚ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን በመፈተሽ ለቀጣይ ስራ ለመዘጋጀት የሚያስችል ነው።
በነዚህ ወራት በሁሉም ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፥ መድረኩ የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ድክመቶችን ለመቅረፍ ያለመ ነው ብለዋል።
ተቋማት በሚያከናውኗቸው ተግባራት ማህበረሰቡን ምን ያህል ተጠቃሚ አድርገዋል የሚለው ጉዳይ በግምገማው ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡