የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች መሸርሸር በሚሊየን የሚቆጠር ህይወትን አደጋ ላይ ጥሏል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

By Adimasu Aragawu

October 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች መሸርሸር በሚሊየን የሚቆጠር ህይወትን አደጋ ላይ ጥሏል አሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፡፡

151ኛው የዓለም የፓርላማ ሕብረት (አይፒዩ) ጉባኤ በችግር ጊዜ የሰብአዊነት ድንጋጌዎችን ማክበር እና የሰብአዊ ርምጃዎችን መደገፍ በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር የጋራ ሰብአዊነታችን መሠረት የሆነው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ መሸርሸር በሚሊየን የሚቆጠር ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል ብለዋል፡፡

ድንጋጌዎቹ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ተጽዕኖ ውስጥ መግባታቸውንና በዓለም ዙሪያ ሲቪሎች፣ የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች እና የሕክምና ባለሙያዎች በግጭት እና በአመጽ እየተጎዱ መሆናቸውን አንስተዋል።

የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ማክበር ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን ሥነ ምግባራዊ ግዴታ ነው ያሉት አፈ ጉባኤው÷ ፓርላማዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሁኑ ወቅት እነዚህን መርሆች የመጠበቅ፣ የባለ ብዙ ወገን ግንኙነት የማጠናከር፣ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲጠበቁና በበቂ ሁኔታ እንዲደገፉ ለማድረግ የሞራል እና የፖለቲካ ግዴታ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከድንጋጌዎቹን በፅኑ እንደምታከብር እና አራቱን የጄኔቫ ስምምነቶችንና ተጨማሪ ፕሮቶኮሎችን የሕገመንግሥቱ እና የሌሎች ሕጎች አካል ማድረጓን መግለፃቸውን የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!