የሀገር ውስጥ ዜና

የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከባለፈው ጉብኝት በኋላ የሚለካ የሥራ እድገት አሳይቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

October 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ባለፈው ከነበረኝ ጉብኝት በኋላ የሚለካ የሥራ እድገት ታይቶበታል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ የጀመርነው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመጎብኝት ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ባለፈው ከነበረኝ ጉብኝት በኋላ የሚለካ የሥራ እድገት ታይቶበታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ የግድቡ ከፍታ 128 ሜትር መድረሱን ተናግረዋል።

አጠቃላይ የሲቪል ሥራውም 70 ከመቶ መድረሱን ገልጸዋል።

ይህ ስኬት ለኃይል ምንጭ ዋስትናችን ላለን ያላሰለሰ ጽኑ ጥረት ምስክር የሚሆን ነው ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!