አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከሚገኙ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይቷል።
ውይይቱ ሚዲያዎች በክልሉ ለሚካሄደው ምክክር ግንዛቤ በማስጨበጥ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ እንዳሉት፥ ከዚህ ቀደም በክልሉ ከሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ምሁራን እና ባለድርሻዎች ጋር ውይይቶች ተካሂዷል።
ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር የተደረገው ውይይትም የዚሁ አካል ነው ብለዋል።
ሚዲያዎች የምክክሩ አስፈላጊነትን፣ የኮሚሽኑ ሥራ አሁን ያለበትን ደረጃ እንዲሁም የምክክር ሂደቶችን ለሕብረተሰቡ በማስገንዘብና ግልጽነትን በመፍጠር ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል።
በምክክር ሂደቱ ዙሪያ በሕብረተሰቡ ዘንድ መተማመንን በመፍጠር ረገድ የክልሉ ሚዲያዎች እገዛ ማድረግ እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ አቶ ጥበቡ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
በመድረኩ ማሕበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በሁሉም የሚዲያ አማራጮች የሚሰሩ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ምክክሩን ለማካሄድ አመቺ ሁኔታዎችን የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!