አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ባለፉት ሶስት ወራት 1 ሺህ 723 ኪሎ ግራም ወርቅ ከክልሉ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገብቷል አለ።
የቢሮው ኃላፊ ቱጃኒ አደም እንዳሉት÷ በ2018 በጀት ዓመት ከ7 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡
በሩብ ዓመቱም የአምራችነት ፍቃድ ካላቸው እና ከልዩ አነስተኛ ማህበራት 1 ሺህ 723 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ተናግረዋል።
ዘርፉ ከሚያስገኘው የተለያዩ የገቢ አማራጮች 27 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡
በተለይም መንግሥት ያደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የጥቁር ገበያ ችግርን በመቅረፍ በዘርፉ የተሰማሩ የወርቅ አቅራቢዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የአምራቾችን ግንዛቤ የማሳደግ እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ሥራ ላይ በስፋት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!