አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ነገሌ አርሲን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አቡበከር አዳሙ እና በፍቃዱ አለማየሁ አስቆጥረዋል፡፡
ነገሌ አርሲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ገ/መስቀል ዱባለ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከፋሲል ከነማ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወቱ ሲሆን÷ ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ ከተማ ደግሞ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል፡፡